Ethio-US trade fair June 25-26, 2021

ethioporomotionllc.com
ethioporomotionllc.com
  • HOME
  • WELCOME
  • ABOUT US
  • ETHIO-US TRADE FAIR
    • EVENT PLANNING
    • TOURISM
    • ENVIRONMENT
  • PARTNERS
  • GALLERY
  • BLOG
  • SUBSCRIBE
    • HOME
    • WELCOME
    • ABOUT US
    • ETHIO-US TRADE FAIR
    • PROJECT
      • EVENT PLANNING
      • TOURISM
      • ENVIRONMENT
    • PARTNERS
    • GALLERY
    • BLOG
    • SUBSCRIBE
  • HOME
  • WELCOME
  • ABOUT US
  • ETHIO-US TRADE FAIR
  • PARTNERS
  • GALLERY
  • BLOG
  • SUBSCRIBE

Ethio-US Tradefair

ኢትዮ ፕሮሞሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት ሊያዘጋጁ ነው

ኢትዮ ፕሮሞሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት ሊያዘጋጁ ነው

ኢትዮ ፕሮሞሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት ሊያዘጋጁ ነው

እና ኢትዮ ፕሮሞሽን በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። ስምምነቱን የፈረሙት ከምክር ቤቱ በኩል

  

እና ኢትዮ ፕሮሞሽን በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። ስምምነቱን የፈረሙት ከምክር ቤቱ በኩል ዋና ፀሀፊ የሱፍ አደምኑር ሲሆኑ የኢትዮ ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አበበ ፈለቀ ናቸው፡፡

በፊርማው ስነ ስረዓት ላይ የምክር ቤቱ ዋና ፀሀፊ እንዳሉት ኤግዚቢሽኖችን፣ አቻለአቻ የቢዝነስ ስብሰባዎች እና የተለያዩ የኔትወርኪነግ ግንኙነቶችን በማዘጋጀት እንዲሁም ከውጭ የሚመጡ ባለሀብቶችን በመቀበል ፣ የሀገር ውስጥ የቢዝነስ ተልኦኮዎችን ወደ ውጪ አገሮች ይዞ በመሄድ እና መሰል ተግባራትን በማከናወን ምክር ቤቱ ከተቋቋመበት ዋነኛ አላማዎች አንዱ የሆነውን የንግድና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ጥረት ያደርጋል፡፡

ከዚህ ቀደም ምክር ቤቱ በራሱም ሆነ ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት በየአመቱ ንግድ ትርኢቶችን ሲያዘጋጅ የነበረ መሆኑን አስታውሰው በእለቱ የሚደረገው የመግባቢያ ስምምነት ደግሞ በቀጣይ አሜሪካ የሚካሄደውን ኤግዚቢሽን ከኢትዮ ፕሮሞሽን ጋር በትብብር ለማዘጋጀት እና ሚሽን ይዞ በመሄድ እዚያ ያለውን ገበያ በተሸለ ሁኔታ ለማወቅ እንዲሁም አሜሪካ የሰጠችንን ከቀረጥ ነፃ የማስገባት እድል (Africa Growth and Opportunity Act - AGOA) የበለጠ ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ፕሮሞሽን ከምክር ቤቱ ጋር ለመስራት መወሰኑን አመስግነው ኤግዚቢሽኑን በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጅትና ለማካሄድ ምክር ቤቱ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ዋና ፀሀፊው አክለው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ምርቶች እየጨመሩ እንደሆነና የታሰበው ኤግዚቢሽንም የበለጠ በማስገባት ረገድ በመጀመሪያዎቹ ተርታ እንደምትመደብ ተገልጿል። አቶ አበበ በበኩላቸው እንደተናገሩት ምክር ቤቱ በርካታ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ያሉት እና እንደዚህ አይነት ኩነቶችን በማዘጋጀት አባላቱን ተጠቀሚ በማድረግ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ጠቅሰው አብረው መስራታቸው ለድርጅታቸውም ሆነ ለምክር ቤቱ የጋራ ጥቅም ያስገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና ኢትዮ ፕሮሞሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከሰኔ 18-19፣ 2013 ለሁለት ቀናት የሚያካሂዱት የንግድ ትርዒትና ባዛር በዋሽንግተን ዲሲ ጌይሎርድ ናሽናል ሪዞርትና ኮንቬንሽን ማዕከል የሚካሄድ ይሆናል።

በዚሁ የንግድ ትርዒት ላይ አስመጪና ላኪዎች፣ አገልግሎት ሰጭዎች ፣ አምራቾች ፣ የፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች የንግድ ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። የንግድ ትርኢቱ፤ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የአፍሪካ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቅደው ህግ ሙሉ ተጠቃሚ ማድረግን፣ ለአሜሪካ የንግድ ተቋማት እና የንግድ ማህበረሰብ መሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ግንዛቤ ማስጨበጥንና ለኢትዮጵያ ምርቶች እና አገልግሎቶች የአሜሪካን ገበያ ተደራሽነት የመፍጠር አላማዎችን የሰነቀ ነው። ከዚህ ሌላ የዝግጀቱ ታዳሚዎች የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያገኙባቸውና እውቀትና ልምዳቸውን የሚለዋወጡባቸው ወርክሾፖችና የውይይት መድረኮችም ተመቻችተዋል። የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነጥበብና ታሪክ የሚያስተዋውቁ መሰናዶዎችም ከዝግጀቱ አካል ናቸው ተብሏል።

ይሄ የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያን የንግድ ማህበረሰብ እጅግ ሰፊ ከሆነውና አሜሪካ ነዋሪ ከሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ትልቅ መድረክ ሲሆን፤ የትውልደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ የፋይናንስ፣ የሪል ስቴት እና የሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ግንዛቤ የሚጨብጡባቸው መድረኮችም ይዘጋጃሉ።

Find out more

ETHIO-US TRADE FAIR

ኢትዮ ፕሮሞሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት ሊያዘጋጁ ነው

ኢትዮ ፕሮሞሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲሲ የንግድ ትርዒት ሊያዘጋጁ ነው

image188

JUNE 25-26, 2021

Copyright © 2021 ethioporomotionllc.com - All Rights Reserved.

Powered by GoDaddy

  • CONTACT US